ኅብረ ዘማሪያኑን ይቀላቀሉ
የኢትዮጵያ የሰላም ኅብረ ዘማሪያን ጓድ በአሁኑ ወቅት ለ2010/2011 የክንዋኔ ወቅት 80 ዘማሪያንን በመመልመል ሂደት ላይ ሲሆን፣ ፍላጎት ያላቸው ዘማሪያን በሙሉ እንዲያመለክቱ ይጋብዛል፡፡ በየትኛውም የክህሎትና ልምድ ደረጃ ላይ ያሉ፣ ከ17 ዓመት በላይ የሆኑ ወንዶችና ሴቶች እንዲሳተፉ እንፈልጋለን፡፡ የመረጣ ሂደቶች ህዳር ወር 2010 ወሩን ሙሉ ይካሄዳሉ፡፡
መስፈርቶች / ከተመልማዮች የሚጠበቁ
የመዘመር እንዲሁም የአካታችነትና በሙዚቀኝነት ልቆ የመገኘት እሴቶቻችንን ተግባራዊ የማድረግ ፍላጎት
በየሳምንቱ (ረቡዕዎች 11፡00 እስከ 1:00) በሚካሄዱ ልምምዶችና በበጋ ወራት በሚካሄዱ ሁለት ትርዒቶች ላይ ለመገኘት ቁርጠኛ መሆን
የመረጣ ሂደቱን በስኬት ማለፍ
የመረጣ ሂደት፡
የመረጣው ሂደት ከኢትዮጵያ የሰላም ኅብረ ዘማሪያን ቡድን ዳይሬክተር ጋር የሚደረግ ከ5 እስከ 10 ደቂቃዎች የሚወስድ ቆይታን ያካትታል፡፡ አይጨነቁ -ከባድ አይደለም! በቃ፣ ድምጽዎን ለመስማትና ሙዚቃዊ ደመ ነፍስዎን ለማወቅ የሚያስችል ዕድል እንዲሰጡን ብቻ ነው የምንሻው፡፡ የመረጣ ሂደትዎ በሚከተለው አኳኋን ነው የሚከናወነው፡
የሚገኙበትን አድራሻ እና ግላዊ መረጃዎን አጠር ባለ ቅጽ ላይ ይሞላሉ
ራስዎን ያስተዋውቁና ከዳይሬክተሯ ጋር ተገናኝተው ይነጋገራሉ
የድምጽዎን እርከን እና ስልት ለመረዳት እንዲያስችለን በዳይሬክተሯ እየተመሩ ጥቂት የድምጽ ልምምዶችን ይጫወታሉ ወይም ይዘምራሉ
ዳይሬክተሯ የሙዚቃ ክህሎትዎን ማወቅ እንድትችል የሚያግዙ ጥቂት አጫጭር ልምምዶችን/ ሙከራዎችን ያደርጋሉ
ተደጋግመው የሚጠየቁ ጥያቄዎች፡
[የ]ሙዚቃ [ኖታ] ማንበብ የማልችል ከሆነስ?
ሙዚቃ የማንበብ ክህሎት የግድ አስፈላጊ አይደለም፡፡ እንዲያውም፣ አሁን ሙዚቃ ማንበብ ለማይችሉ ሰዎች ሙዚቃ የማንበብ ክህሎት ትምህርት ይሰጣቸዋል! በሌላ በኩል፣ ሙዚቃ በተሟላ ሁኔታ ማንበብ የሚችሉ ሰዎች፣ ሙሉ በሙሉ በሙዚቃ ማንበብ ላይ ትኩረት በሚያደርገው የልምምዶቹ የመጀመርያ ክፍል አለመካፈል ይፈቀድላቸዋል፡፡
ልምምዶች በምን ቋንቋ ነው የሚካሄዱት?
ልምምዶች በእንግሊዝኛ የሚመሩ ሲሆን፣ ወደ አማርኛ ይተረጎማሉ፡፡ ምንም እንኳ አብረን በምንቆይባቸው ጊዜያት የተወሰነ እንግሊዝኛ ማወቅዎ እንደማይቀር እርግጠኛ ብንሆንም፣ በኢትዮጵያ የሰላም ኅብረ ዘማሪያን ቡድን ውስጥ ስኬታማ ለመሆን ግን እንግሊዝኛ መናገር አያስፈልግዎትም፡፡
ለመጓጓዣ የሚሆን ገንዘብ ይሰጣልን?
በኢትዮጵያ የሰላም ኅብረ ዘማሪያን ቡድን ውስጥ ለሚሳተፉ ዘማሪያን ወደ ልምምድ ቦታ የመምጫና ከልምምድ ቦታ ወደ ቤት የመጓጓዣ ወጪን የሚሸፍን የመጓጓዣ አበል ይሰጣል፡፡ የመጀመርያውን ምዕራፍ ልምምድ በብቃት የሚያልፉ ተሳታፊዎች ተጨማሪ መረጃ ያገኛሉ፡፡
How to join the Ethiopian Peace Choir
The Ethiopian Peace Choir is now recruiting 80 singers for its 2017/2018 season and invites all enthusiastic singers to apply. We are seeking men and women, ages 17+, of all experience levels. Auditions will be held throughout November of 2018.
qUALIFICATIONS/EXPECTATIONS
A desire to sing and practice our values of inclusivity and musical excellence
Commitment to weekly rehearsals (Wednesdays from 5:00-7:00pm) and two Spring performances
A successful audition
auditions
Your audition will consist of a 5-10 minute meeting with the Director of the Ethiopian Peace Choir. Don't worry- it's casual! It's simply a chance for us to hear your voice and get to know your musical instincts. Your audition will go as follows:
Fill out a brief form with your contact and personal information
Introduce yourself and meet the Director
Sing a few vocal exercises led by the Director so we can learn your vocal range and style
Do a few brief exercises to help the Director know your musical capabilities
faq
What if I can't read music?
The ability to read music is not mandatory. In fact, that skill will be taught to those who are currently unable to read music! On the other hand, those who can read music fluently, will be excused from the first portion of rehearsals, which will focus solely on music literacy.
What language will rehearsals be led in?
Rehearsals will be led in English with the help of an Amharic translator. You do not need to speak English to be successful in the Ethiopian Peace Choir, although we think you'll definitely pick some up over the course of the season.
Are there transportation scholarships?
Transportation scholarships are available to singers in the Ethiopian Peace Choir to help defray the cost of getting to and from rehearsals. More information will be available to those who qualify at the first rehearsal.