Ethiopian Peace Choir
 

Music as diplomacy in the Horn of Africa

 
ba54bae0ed97.jpg
 

Mission / ተልዕኮ

The Ethiopian Peace Choir envisions an ensemble in Addis Ababa built from local singers with ethnic origins spanning many or all the Ethiopian Ethnicities- Amharas, Oromos, Tigrayans, Somalis, and others (i.e. Sidama, Gurage, Welayta, Americans, other expats). We will be inclusive and equally welcoming of all participants, regardless of and not limited to ethnicity, religion, and socioeconomic status. We foresee an environment for the chorus which demands excellent musicianship in the performance of repertoire from Ethiopia and around the world, while serving socially as peace ambassadors through the fostering of meaningful relationships with one another and the community.

የኢትዮጵያ የሰላም ኅብረ ዘማሪያን ተልዕኮ፣ በአዲስ አበባ ከአብዛኛዎቹ ወይም ከሁሉም የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች - ከአማራ፣ ከኦሮሞ፣ ከትግሬ፣ ከሶማሊ፣ ከሲዳማ፣ ከጉራጌ፣ ከወላይታ እና ከሌሎችም ብሔረሰቦች፤ እንዲሁም ከአሜሪካውያንና ከሌሎች በኢትዮጵያ ነዋሪ የውጭ ሀገር ዜጎች - በተውጣጡ ዘፋኞች የተገነባ የሙዚቃ ቡድን ዕውን ማድረግ ነው፡፡ በቡድናችን ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች በብሔር፣ በሃይማኖት እንዲሁም በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ደረጃ ሳንለይ፣ በእነዚህም ሳንገደብ እናካትታለን፤ ሁሉንም ተሳታፊዎችም በእኩልነት እናስተናግዳለን፡፡ የኅብረ ዝማሬ ቡድኑ ከኢትዮጵያና ከዓለም ዙርያ ከፍተኛ የሙዚቃ ክህሎት የሚጠይቁና የሚያውቋቸውን ጥበባዊ ሥራዎች የሚከውኑበት ምቹ ከባቢ እንደሚፈጠርላቸውና፣ በተጓዳኝም በማኅበራዊ መስክ እርስ በእርሳቸውና ከማኅበረሰባቸውም ጋር ትርጉም ያለው ግንኙነት በመመሥረት የሰላም አምባሳደር ሆነው ማገልገል የሚችሉበት መድረክ ይፈጠርላቸዋል ብለን እንጠብቃለን፡፡             

Values - P.E.A.C.E. / እሴቶች

Promote and Practice Inclusivity

  • Embody diversity in our choral member make-up

  • Practice understanding and respecting our diverse backgrounds and values

Empower the Community

  • Provide opportunities for singers to perform in a trained, performance ensemble

  • Make choral music accessible to the community through annual concerts

Acquisition of Musical and Leadership Skills

  • Teach basic musicianship and theory skills necessary to be a successful choral reader

  • Provide leadership positions and mentorships for participants seeking to be actively involved in the development of the chorus

Celebrate Music from Around the World

  • Present the music of Ethiopia alongside repertoire from across the globe

Excellence in Musicianship

  • Seek the highest level of artistic achievement

አካታችነትን / ልዩነት ባለመፍጠር  ማራመድና መተግበር

  • በኅብረዝማሬ ቡድናችን የአባላት ስብጥር ብዝኃነትን መግለጽ

  • የተለያዩ ዳራዎችና እሴቶች ያሉን መሆኑን መገንዘብና ለዚህም አክብሮት መስጠትን በተግባር ማሳየት

ማኅበረሰብን ማብቃት

  • ለዘፋኞች ከሰለጠነ የኪነት ቡድን ጋር የመጫወት ዕድል መስጠት

  • በዓመታዊ የሙዚቃዝግጅቶች አማካይነት ማኅበረሰቡ የኅብረ ዝማሬ ሙዚቃ መታደም የሚችልበትን ዕድል መፍጠር

 የሙዚቃ እና የአመራር ክህሎት ማግኘት

  • ስኬታማ የኅብረ ዝማሬ መሪ ለመሆን የሚያስፈልጉ መሠረታዊ የሙዚቀኝነት እና የንድፈ ሐሳብ ክህሎቶችን ማስተማር

  • የኅብረ ዝማሬ ቡድኑን በማሳደግ ተግባር ላይበንቃት መሳተፍ ለሚፈልጉ ተሳታፊዎች የአመራር ቦታዎችን እና የአሰልጣኝነት ብቃት ማጎናፀፍ

ከዓለም ዙርያ ለሚመጡ ሙዚቃዎች ክብርና ዋጋ መስጠት

  • የኢትዮጵያን ሙዚቃ ከዓለም ዙርያ ከሚመጡየሙዚቃ ሥራዎች ጋር አብሮ ማቅረብ

በሙዚቀኝነት ልቆ መገኘት

  • በኪነ ጥበባዊ ስኬት ከፍተኛውን ደረጃ ለመቀዳጀት መሻት